Asteryo Media Media - አስተርዮ ሚዲያ
በዚህ የፌስ ቡክ ገፅ መንፈሳዊ ፣ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ኩነቶች የዜና ዘገባዎች ይተላለፋሉ።
04/04/2026
!!
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ ጥንተ ስቅለት እና የሆሳዕና በዓል በአርባ ምንጭ!
"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን"። ት.ኢ ፶፫፥፷
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ካቴድራል የሚከበረውን ታላቅ ዓመታዊ የንግስ በዓል ምክንያት በማድረግ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት እና የዐብይ ጾም ፰ኛው ሳምንት ሆሳዕና በዓል ነው። ሁለቱ ታላላቅ በዓላት በአንድ ዕለት የሚከበሩበት ልዩ መንፈሳዊ አጋጣሚ ሲሆን
በእለቱ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ (የጋሞና አካባቢው፣ የጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል) በመካከላችን በመገኘት በዓሉን ይባርካሉ።
በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።
የአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ካቴድራል ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
04/04/2026
04/04/2026
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ |ሥልጣነ ክህነት ሲሰጡ ያስተላለፉት መልዕክት| መጋቢት ፳፮/፳፻፲፰ ዓ/ም ብፁዕ አቡነ ኤልያስ |ሥልጣነ ክህነት ሲሰጡ ያስተላለፉት መልዕክት| መጋቢት ፳፮/፳፻፲፰ ዓ/ም
11/03/2026
ከብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞና አካባቢው ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተሰጠ የሐዘን መግለጫ
-------
(ብፁዓን እለ ይላሕው ይእዜ እስመ እሙንቱ ይትፌሥሑ፡፡)
“የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መፅናናትን ያገኛሉና፡፡'' (ማቴ.፭፤፬)
ትናንት በጋሞ ዞን በተለያዩ ደጋማ አካባቢዎች ማለትም በጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ፣ በላካ፣ በቦንኬ ወረዳ የላ ቀበሌ እንዲሁም በከምባ ዙሪያ ወረዳ ባልታ ቀበሌዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉን፣ እንዲሁም በአርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያው የኩልፎና ስጎ ወንዞች መሙላት በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን በታላቅ ሐዘን ሰምተናል።
ይህ ድንገተኛ አደጋ በወገኖቻችን ላይ ያደረሰው የሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ለመላው የአካባቢው ነዋሪና ለቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ መርዶ ነው።በመሆኑም በራሴና በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ስም እንዲሁም በመላው የኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን ስም የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልጻለን፡፡
በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት እንዲያሳርፍልን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥ እንጸልያለን። በንብረታቸው ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ፈጣሪ ጥንካሬውን እንዲሰጣቸው እንመኛለን፡፡
ሀገረ ስብከታችን ይህንን አስከፊ ወቅት ለማለፍና የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ማንኛውም ዓይነት ሰብአዊ ድጋፍና መርሐ ግብሮች ላይየበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡።
መላው ሕዝባችንም የተጎዱትን በመርዳትና በማጽናናት የወንድማማችነትና የአብሮነት እናስተላልፋለን። የቆየውን እሴቱን በተግባር እንዲያሳይ ጥሪያችንን
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝባችንንና ምድራችንን ከክፉ መከራ ሁሉ ይጠብቅልን !!
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ
የጋሞና አካባቢው፣ ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል !!
መጋቢት ፪/፳፻፲፰ ዓ.ም
አርባ ምንጭ
Category
Contact the business
Telephone
Address
Arba Minch
Arba Minch'
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Asteryo Media Media - አስተርዮ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.