Mltmase

Mltmase

Share

Communication

15/09/2022
22/06/2022

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ያላቸውን አጋርነት በተግባር እያሳዩ ነው
**************

ክልሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ይደግፉ ወንድማማችነትን ያጠናክሩ በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በህዳር 14/2014 ዓ.ም የፌዴሬሽኑ 11ኛ ክልል ሆኖ የተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአጭር ወራት ውስጥ በርካታ የህብረተሰቡን ጥያቄዎች መፍታት መቻሉን የተናገሩት የክልሉ ም/ር/መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ አንጻራዊ ሰላም መፍጠር መቻሉንም አንስተዋል።

ክልሉ የአጋሮች ድጋፍን በፈለገበት በዚህ ወቅት ክልሎች ላሳዩት ቀና ምላሽም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለክልሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 50 ሚሊዮን፣ የአማራ ክልል 50 ሚሊዮን፣ ደቡብ ክልል 30 ሚሊዮን፣ ሲዳማ 20 ሚሊዮን፣ ሶማሌ 20 ሚሊዮን፣ ቤንሻንጉል 10 ሚሊዮን፣ አፋር 10 ሚሊዮን፣ ጋምቤላ 5 ሚሊዮን፣ ሐረሪ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ሚድሮክ ኢትዮጵያም ለክልሉ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ደግሞ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለክልሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

በተጨማሪም የተለያዩ የግል ተቋማት እና የግል ድርጅቶችም ለክልሉ ድጋፍ እያደርጉ ነው።

እስካሁን ባለው መረጃ ለክልሉ ከ697 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ቃል ተገብቷል።

በአሸናፊ እንዳለ

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

02/06/2022
27/05/2022

በኢትዮዽያን የመሩ መሪዎች ( Leaders)በሙሉ ባለቤቶቻቸው (ሚስቶቻቸው) ከአንድ አካባቢ ወይም ክልል ወይም ብሔር ናቸው ግጥምጥሞሽ ወይስ?
1-ዝናሽ ታያቸዉ(ጎንደር) አብይ አህመድ
2-ሮማን ተስፋዬ(ጎንደር) ሃ/ማርያም ደሳለኝ
3-አዜብ መስፍን(ጎንደር) መለስ ዜናዊ
4-ውባንቺ ቢሻው(ጎንደር) መንግስቱ ሀ/ማርያም
5-መነን አስፋው (ጎንደር) ሀይለ ስላሴ
6-ጣይቱ ብጡል (ጎንደር) ምኔሊክ፪
ወዘተርፈ…
እናም መሪ መሆን ከፈለጉ አንዱ መመዘኛ ይሄ ነው ማለት ነው?!
ምንጭ:- FB

22/05/2022

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ።

አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እንድትሆን እና ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ የሕንጻዎችን ቀለምና ቁመት የሚወስን አሠራርን መተግባር መሆኑን አስታውቋል።

በእስካሁኑ ሂደት የከተማዋ ሕንጻዎች ያለምንም ቁጥጥርና ወጥነት በጎደለው መንገድ የሚቀቡ ቀለማት የከተማዋን መልክ ቡራቡሬና ዥንጉርጉር ከማድረጋቸውም በላይ÷ የሚገነቡ ሕንጻዎች ዲዛይን በዘፈቀደ መሠራቱ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ ጎድቶታልም ነው ያለው አስተዳደሩ፡፡

ስለሆነም ይህን ችግር መልክ ለማስያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዙ ዓለም አቀፍና አፍሪካዊ ከተሞች ተሞክሮ በመውሰድ÷ ለከተማዋ የሚስማማ የሕንጻ ቀለማት ደረጃን አጥንቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡

በመሆኑም በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ሁኔታ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል።

በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን÷ ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ መገባቱንም ነው ያስታወቀው፡፡

የተመረጡት ቀለሞች የሚከተሉት ናቸው፦

Category

Telephone

Website

Address


Adiss Ababa _Alaba Kulito
Alaba K'ulito
123

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mltmase posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Alaba K'ulito.