Dalol Medical and Surgical Center

Dalol Medical and Surgical Center

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dalol Medical and Surgical Center, Health/Beauty, Kembolcha.

Photos from Kombolcha city  communication's post 13/09/2026
11/09/2026

እንኳን ለ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሰን፡፡

መልካም አዲስ ዓመት!

ዳሎል የህክምና ማዕከል፤ ወሎ ኮምቦልቻ!

Photos from Dalol Medical and Surgical Center's post 11/08/2026

ሰለ ጉበት ቫይረስ በሽታ
*** ዳሎል የህክምና ማዕከል ***

👉የጉበት ቫይረስ በሽታ በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሰዎችን እያጠቃ የሚገኝ ህመም ነው። በአጠቃላይ 5 አይነት የጉበት በሽታ ቫይረስ አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም ሄፓታይተስ ኤ፤ቢ፤ሲ፤ዲ እና ኢ ይባላሉ፡፡

👉ከእነዚህ ውስጥ ግን ረጅም ጊዜ የሚቆይ በሽታን በማምጣት የሚታወቁት ቢ እና ሲ የተባሉት ሲሆኑ ሄፓታይተስ ቫይረስ ዲ እና ኢ ደግሞ ብዙም የተለመዱ አይደሉም፡፡

👉ያልጠናበት ህመምተኛ የሚያሳያቸውን ምልክቶች ስናይ ትኩሳት፤ ድካም ድካም የማለት ስሜት ፤ማቅለሽለሽ፤የምግብ ፍላጎት ማጣት፤የሰውነት ሽፍታ እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም ሲሆኑ ትኩሳቱ በጊዜ ሂደት እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን በስተመጨረሻም የታካሚው ሰውነት እና አይኖች ቢጫ መሆን ሊኖር ይችላል፡፡የጠና የጉበት ህመም በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ግን በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩም እንደ ድካም እና የመዛል ስሜት ይስተዋልባቸዋል፡፡

👉በሽታው ሳይታከም ከቆየ ወደ ማይመለስ የጉበት በሽታ ወይም በህክምና አጠራሩ Cirrhosis እና የጉበት ካንሰር ሊለወጥ ይችላል፡፡ታማሚው ያለበትን የጉበት ቫይረስ ዐይነት ለመለየት ቀለል ያለ የደም ምርመራ ማድረግ ይቻላል፡፡

የእያንዳንዱን አይነት የጉበት በሽታ በዝርዝር ስናይ፡

👉HEPATITIS B ሄፓታይተስ ቢ፡-ሄፓታይተስ ቢ ሲርሆሲስ እና የጠና የጉበት ህመም በማምጣት ይታወቃል፡፡መተላለፊያ መንገዶቹን ስናይ እንደ መርፌ እና ምላጭ የመሳሰሉ የተበከሉ ስለታማ ነገሮች፤ከእናት ወደ ልጅ እና የገብረ ስጋ ግንኙነት ይጠቀሳሉ፡፡

የጠና ህመም ያለባቸው በደም ውስጥ የሚገኘውን የቫይረሱን ቁጥር (viral laod) እንዲሁም የጉበት መቆጣትን የሚቀንሱ በመርፌ እና በሚዋጥ እንክብል መልክ የሚሰጡ ሲሆኑ ይህም የበሽታውን ወደ ሲርሆሲስ እና የጉበት ካንሰር መቀየር እድሉን ይቀንሳል፡፡

👉HEPATITIS C ሄፓታይተስ ሲ ፡- ልክ እንደ ሄፓታይተስ ቢ ሁሉ ሄፓታይተስ ሲም ለጉበት ካንሰር እና ሲርሆሲስ ለሚባለው የጠና የጉበት ህመም የሚዳርግ ሲሆን መተላለፊያ መንገዶቹም ተመሳሳይነት አላቸው፡፡እስከዛሬ ድረስ ሄፓታይተስ ሲ ን ለመከላከል፤ የሚያገለግል ክትባት ያልተገኘ ሲሆን ሄፓታይተስ ሲ በሽታ ታማሚዎችም የተለየ የሚያሳዩት ምልክት የለም ።

-----ጠቃሚ ምክሮች በጉበት ህመም ለተጠቁ----
- የአልኮል መጠጥን እና ሲጋራ ማጨስ ማቆም
- ማንኛውንም አይነት መድኃኒት ከመውሰዳችን በፊት ለጉበት ጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን ማረጋገጥ
- የባህል መድኃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ
- በቂ እረፍት ማድረግ
- ጫና የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ መቆጠብ
- እንደ ሲርሆሲስ እና የጉበት ጮማ መኖራቸውን ለማረጋገጥ በየጊዜው ክትትል ማድረግ
- ከታማሚው ጋር በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ክትባት መውሰድ
- ህክምና ጀምረው ከሆኑ ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ህክምናዎትን በሚገባ መከታተል ያስፈልጋል ።
- የተጠቃ ቤተሰብ ካለ እርግዝና ላይ ወደ ፅንስ እንዳይተላለፍ ሀኪምን ማማከር፤ ወደ ሌሎች የቤተሰብ አባል እንዳይዛመት ቅድመ ጥንቃቄ እና ህክምና ማድረግ
-

ለተጨማሪ ማማከር፥ ህክምና እና ክትትል የህክምና ማዕከላችንን ይጎብኙ።

ዳሎል የህክምና ማዕከል፡ ወሎ ኮምቦልቻ!

Category

Website

Address

Kembolcha

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dalol Medical and Surgical Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Kembolcha.