Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola

Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola, Health/Beauty, Daarra, Dilla.

26/09/2026

እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከዳራ ወረዳ ባ/ቱ/ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
መስከረም 16/2019ዓ.ም
ዳራ ወረዳ ባ/ቱ/ስፖርት ጽ/ቤት

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

መስቀል በዓል በኢትዮጵያ ውስጥ ከክርስትና እምነት፣ ከታሪክ፣ ከባህል እና ከማኅበራዊ አንድነት ጋር በጥልቅ የተያያዘ በዓል ነው።
መስቀል በክርስትና እምነት መሠረት፣ መስቀል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን መከራን ተቀብሎ የተሰቀለበትን እና የትንሣኤውን ተስፋ የሚያስታውስ ዋና የክርስትና ምልክት ነው። ስለዚህ ለክርስቲያኖች መስቀል የሚወክለው፦የክርስቶስ መስዋዕትነት፣የድኅነት ተስፋ፣ፍቅርና ይቅርታ፣እምነትና ትዕግሥትነው።

በተለይ የደመራ ሥነ-ሥርዓት የመስቀል በዓል ልዩ መገለጫ ነው።
በኢትዮጵያዊ የክርስትና ትውፊት መሠረት፣ ደመራ ከቅዱስ መስቀል መገኘት ትርክት ጋር ይያያዛል። የደመራ እሳት ሲነድ ሕዝቡ በጋራ ይዘምራል፣ ይደሰታል፣ ጸሎትም ያደርጋል።ይህም እምነት፣ ተስፋ፣ ደስታና የማኅበረሰብ አንድነት የሚገልጽ ባህላዊ መገለጫ ሆኗል።
ዋናው መልእክት የመስቀል በዓል ለክርስቲያኖች የሚያስታውሰው ትልቁ መልእክት ከመከራ በኋላ ተስፋ፣ ከጨለማ በኋላ ብርሃን፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር እና ከመለያየት ይልቅ አንድነት ነው የሚገልፀዉ።

ስለዚህ መስቀልን ስናከብር የታሪክ ክስተትን ብቻ ሳይሆን፣ የእምነት፣ የተስፋ፣ የፍቅር እና የሰላም መልእክትን እናስታውሳለን።

‎በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
‎
‎ መልካም በዓል!
‎
‎

Photos from Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola's post 17/09/2026

ዳራ ወረዳ ባ/ቱ/ስፖርት ጽ/ቤት ከክልልና ከዞን የመጡ እንግዶች ''ጎጅ ልማዳዊ ድርግቶች'' ላይ የተሰሩ ስራዎች እና መልካም ተሞክሮ በጽ/ቤቱ ሐላፊ በኩል ቀርቦ ልምድ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል።
መስከረም 7/2019ዓ.ም
ዳራ ቀባዶ

10/09/2026

ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ባ/ቱ/ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ማቲዎስ ለ 2019ዓ.ም ለአድሱ አመት እንኳን በሰላም አደረሳችው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጳጉሜ 5/13/2018
ዳራ ወረዳ ባ/ቱ/ስፖርት ጽ/ቤት

ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ባ/ቱ/ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ማቲዎስ ለ 2019ዓ.ም ለአድሱ አመት እንኳን በሰላም አደረሳችው አደረሰን መልዕት አስተላልፈዋል።

በመልዕታቸው የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መልካሙ ማቲዎስ ባሳልፈነዉ አመት በወረዳችን በባህል ዘርፍ እና በስፖርቱ ዘርፍ በርካታ ስከቶችን አስመዝግበናል።

የብልጽግና ፓርትያችን በመደመር እሳበ በመፍጠርና በመፍጠን የልማት ትሩፋቶቻችን በርካታ ህዝባችን ተጠቃም ማድረግ ችለናል።

በሁለቱ ዘርፍ ማለትም በባህል እና ቱርዝም ዘርፍ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ስሆን የመስብ ቦታዎችን ከማስተዋወቅ ጀምሮ በክልልና በፈዴራል መንግሥት ድጋፍ እንድለሙ የቱርዝም ሳይቶችን ሰለክት ተደርጓል:: በስፖርቱ ዘርፍም ከወትሮ በተለየ ሁነታ በክረምት ልዩ ልዪ ስፖርት÷ በዞን ደረጃ በተደገው ባህል ስፖርት ውድድር ላይ 1ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ በርካታ ድሎች ተመዝግበዋል። ህዝባችን በስፖርቱ እንድታደሙ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ውጤትም አምጥተናል።

አድሱን አመት ስናከብር የተቸገሩት በማሰብ፣የታረሱት በማልበስ ማዕድ በማጋራት የመረዳዳት ሰራ ከዋዘማው ጀምሮ በየደረጃው ተግባራዊ እንድደረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ይህ አሁን የሚመሰረተው አዲሱ መንግስት የሰላም የልማት መንግስት እንድሆንልን እመኛለሁ በማለት

ይህ አድሱ አመት
የስከት ፣የሠላም፣የከፍታ ፣አመት እንድሆንላችሁ መልክቶን አሰተላልፎዋል።

Photos from Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola's post 08/09/2026

የቀድሞው ሲዳማ ቡና ክለብ ዳራ የወለደችው ስሆን ሌላ ተተኪ ሲዳማ ቡና እንመስርት በማለት ከ13 ዓመት በታች 17ቡድኖችን ያቋቋምን ስሆን 6 ቡድናትን በወረዳ ውስት በተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ለተከታታይ 7 ዓመት ሙሉ ትጥቅ እየገዙ
ከአሰልጣኝ ጭምር ተረክበውናል ዳራ የስዳማ ቡና ክለብ መፍለቂያ በመሆኗ ቀጥላለች ታዳግ ልማታዊ ባለሃብቶች ዳራ ታመሰግናቿለች
➷Daarra Daraari Sidaama Roori!

07/09/2026

✍️ የዳራ ወረዳ የስፖርት ዘርፍ ዓመታዊ አፈጻጸም
ዳራ ወረዳ—የስፖርት ፍቅር ባህል የሆነበት፣ ተስፋ ያላቸው ወጣት ስፖርተኞች የሚፈሩበት እና የስፖርት ተመልካች ማኅበረሰብ የሚኮራበት ወረዳ ነው።
በሲዳማ ክልል የስፖርት ታሪክ ዳራ ወረዳ ልዩ ቦታ አላት። የስፖርት ፍቅር በትውልድ የተላለፈበት፣ የስፖርት ውድድር ከመዝናኛ በላይ የማኅበረሰቡ የአንድነትና የደስታ መገለጫ የሆነበት ማኅበረሰብ ነው። ዳራ ወረዳ ከ“ሲዳማ ቡና” ታሪካዊ መነሻ ጋር የተሳሰረ የስፖርት ትውስታ ያላት በመሆኑ፣ ይህን የስፖርት ባህል ማስቀጠልና ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የዛሬ ትውልድ ኃላፊነት ነው።
✍️ በቀባዶ 4H ሜዳ ላይ የሚከናወኑ የስፖርት ውድድሮች ደግሞ የዚህ ፍቅር ሕያው ምስክር ናቸው። ሴትና ወንድ፣ ሕፃንና አዛውንት የክረምቱን ወቅት በጉጉት የሚጠብቁት፤ ክረምቱ ሲደርስም ኳስን ለመመልከት፣ የ“ዳራ ወረዳ አደገኛ” ህብረ ዜማን እና ሌሎች የድጋፍ ድምጾችን ለመስማት እግሩን ወደ ሜዳ የሚያፈጥንበት የስፖርት ባህል በዳራ ጠንክሮ ቀጥሏል።
አዲስ መነቃቃትና የተጫዋች ማፍራት
ይህን ታሪካዊ የስፖርት ፍቅር ከዘመኑ ፍላጎት ጋር በማጣመር፣ በያዝነው ዓመት ከስፖርት ምክር ቤትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ በመሥራት በወረዳው የስፖርት ዘርፍ አዲስ መነቃቃት መፍጠር ተችሏል።
ዋናው ትኩረትም የዛሬን ውድድር ብቻ ማሸነፍ ሳይሆን፣ የነገን ተስፋ የሚሆኑ ስፖርተኞችን ከታች ጀምሮ ማፍራት ላይ ተደርጓል። በዚህም፦
👉 ከ13 ዓመት በታች 17 ቡድኖች በየቀበሌው ተደራጅተዋል፤
👉 ከ15 ዓመት በታች 8 ቡድኖች ተመስርተዋል፤
👉 ከ17 ዓመት በታች 6 ቡድኖች ተደራጅተዋል፤
👉 5 የጤና ስፖርት ቡድኖች ተቋቁመዋል፤
በደጋማው ቀበሌ የሩጫ ፕሮጀክት በሴቶችና በወንዶች ተጀምሯል፤
የመረብ ኳስና የባህል ስፖርት ውድድሮችም በተደራጀ መልኩ ተካሂደዋል።
ይህም ስፖርትን ከአንድ የውድድር ዓይነት አሻግሮ፣ ልጆችን ከታች ጀምሮ በማሳደግ፣ ወጣቶችን በማሳተፍና ማኅበረሰቡን በማነቃቃት የስፖርት ሥርዓቱን የሚያጠናክር መሠረት ፈጥሯል።

✍️ የስልጠናና የውድድር ውጤቶች
የተጀመረው ሥራ በስልጠና እንዲዳብርና ተሰጥኦዎች ወደ ውጤት እንዲቀየሩ በመሥራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በባህል ስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ የዞን አንደኛ ደረጃን ማግኘት ተችሏል። በተጨማሪም ከ15 ዓመት በታች የክልል ውድድር ላይ 6 ወንድና 10 ሴት ስፖርተኞች እንዲወከሉ ማስመረጥ ተችሏል።
👉 በሴቶች እግር ኳስ በዲላ በተካሄደው ውድድር ወረዳው አሸናፊ ሆኗል። በተለያዩ ውድድሮችም ዳራ ወረዳ ግምባር ቀደም ተሳታፊና ተወዳዳሪ ሆና መቅረቧ የዘንድሮ የስፖርት ሥራ ተጨባጭ ፍሬ እያፈራ መሆኑን ያሳያል።


✍️ የዘንድሮው ክረምት ውድድር ደግሞ በዳራ የስፖርት ታሪክ ልዩ ትውስታ የሚሆን ሆኗል። 38 ቡድኖች ተሳትፈውበት፣ ለ26 ቀናት በደመቀ የውድድር መንፈስ የተካሄደው ይህ መርሃ ግብር እስከ ፍጻሜው ድረስ የማኅበረሰቡን ትኩረትና ድጋፍ ማግኘት ችሏል።
የፍጻሜ መርሃ ግብሩም ከ13 ዓመት በታች፣ ከ17 ዓመት በታች፣ የጤና ስፖርት በእግር ኳስ፣ የሴቶች እግር ኳስ፣ የቀበሌ እግር ኳስ፣ መረብ ኳስና ባህል ስፖርትን በማካተት የዳራን የስፖርት ብዝሃነትና የማኅበረሰቡን ተሳትፎ በአንድ መድረክ አሳይቷል።


የዘንድሮ ውጤት የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን፣ ለቀጣዩ የስፖርት ልማት የተጣለ መሠረት ነው። የተጀመሩትን የሕፃናትና ወጣቶች የስፖርት ፕሮጀክቶች በማጠናከር፣ የስልጠና አቅምን በማሳደግ፣ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በመለየትና በማሳደግ ብዙ ተስፋ ያላቸው ስፖርተኞችን ማፍራት ይጠበቃል።
በተጨማሪም ቀበሌዎች የስፖርት እንቅስቃሴያቸውን እንደቀድሞ እንዲያጠናክሩ፣ ሴቶችና ወጣቶች በስፋት እንዲሳተፉ፣ የጤና ስፖርትና የባህል ስፖርት እንዲስፋፋ በማድረግ የዳራን የስፖርት ባህል ወደ አዲስ የልማት ደረጃ ማሸጋገር የቀጣይ ዘመን ተልዕኮ ይሆናል።
✍️ ዳራ ወረዳ ስፖርትን ብቻ አትጫወትም—በስፖርት ተስፋ ትፈጥራለች፤ በወጣቶቿ ችሎታ ትኮራለች፤ በማኅበረሰቧ ተሳትፎም የነገን ድል ትገነባለች።
የዛሬው ውድድር የነገው ሻምፒዮን መነሻ ነው፤ የዛሬው ተሳትፎ የነገው የስፖርት ታሪክ መሠረት ነው።

Photos from Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola's post 06/09/2026

በዳራ ወረዳ ለአንድ ወር ሲካሄድ የከረመው፣ የክረምት ወጣቶች ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ዉድድር ተጠናቀቀ።
**********
ሐዋሳ:-ጳጉሜ 01/13/2018 ዓ/ም

በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ስር በሚገኘው የዳራ ወረዳ አስተዳደር፣ ደረጃ ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ.ም የክረምት ወጣቶች ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በመዝጊያው ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የፋይናንስ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ሚልኪያስ አየለ፣ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ወድድሮች በፋይናንስ ከመደገፍ ባለፈ፥ ውድድሮች ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው እንዲካሄዱ በመምራት እና በቅርበት በመከታተል ረገድ ኮሚሽኑ የአንበሳውን ድርሻ መወጣቱን አስረድተዋል።

የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሀያልነሽ ሀንቃሞ በበኩላቸው፤ ስፖርት ማህበረሰብን ከማህበረሰብ ጋር ከማስተሳሰር እና ሰላምን ከመገንባት ባለፈ፥ አሁን ላይ ትልቅ የገቢ ምንጭ እየሆነ የመጣ ዘርፍ መሆኑን በማንሳት ውድድሩ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ ዞኑ ከወረዳው መዋቅር ጋር በመሆኑ ትልቅ ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ መቆየቱን አብራርተዋል።

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ስፖርተኞች በሰጡት አስተያየት፥ ውድድሩ ብቃታቸውን እንዲያሳዩ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው በመግለፅ፣ እንደዚህ አይነት መሠል ዉድድሮች ወደፊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በመጨረሻም በወረዳ ደረጃ ለአንድ ወር ሲካሄድ በሰነበተው ዉድድር ላይ ላቅ ያለ አፈጻጸም ላሳዩ በየደረጃው ለሚገኙ አካላት እና ተጨዋቾች፣ የምስክር ወረቀት፣ የሜዳሊያ እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Photos from Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola's post 04/09/2026

🏆🏆 ታላቅ የፍፃሜ የዋንጫ ጨዋታ Sport 🏆🏆

✍️ ዕለተ ቅዳሜ ነሐሴ 30/2018ዓ፣ም

and Daarra Woreda Culture,Turisium and sport ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት የክረምት ወራት Sport ውድድር በድምቀት ተካሂዶ እነሆ ወደ ፍፃሜው ደርሷል
✍️ Mass Sport
☝️ ቅዳሜ ነሐሴ 30/2018ዓ፣ም 12:00

👉 Menigist seratenyochi
👉 amerarochi
👉 Projectochi
👉 Martial art Team
👉 Negadewochi
👉 Yepolis serawitochi
👉 Ye Daarra Woreda mahibereseb Hulu yigengali

✍️ Volley Ball Tournament (Ye Mereb kuas የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)
👉 4:00 🆚 ( የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)

✍️ Cultural Tournament (Ye Bahil sport)
👉 Korbo ( የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)
👉 Gebeta ( የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)
👉 Kesit ( የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)
Time 4:00
✍️ U-13 አጓጊው የዋንጫ ጨዋታዎች ለማካሄድ ተዘጋጅቷል።

👉 ቅዳሜ ነሐሴ 30/2018ዓ፣ም 8:00 U-13 Family 🆚 ( የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)

✍️ ዋንጫውን ማን ይወስደዋል? 🏆❓
👉 U-13
🏆 ወይስ Rehobot 🏆?



✍️ ጨዋታዎቹ ቅዳሜ ነሐሴ 30/2018ዓ፣ም 1/2018 ስታድየም በድምቀት ይካሄዳሉ

✍️ ስፖርት ወዳድ የሆናችሁ መላው ማህበረሰብ ስታዲየም በመገኘት ይህንን ታሪካዊ የፍፃሜ ጨዋታ እንድትታደሙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል!

🏆🏆

04/09/2026

🏆🏆 ታላቅ የፍፃሜ የዋንጫ ጨዋታ 🏆🏆
1/2018
and Daarra Woreda Culture,Turisium and sport ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር በድምቀት ተካሂዶ እነሆ ወደ ፍፃሜው ደርሷል


✍️ አጓጊው ውድድር የዋንጫ ጨዋታዎች ለማካሄድ ተዘጋጅቷል።


👉 እሁድ 8:00 .
Mazegaja 🆚 Mubaarik ( የዋንጫ ፍፃሜ 🏆)

✍️ ዋንጫውን ማን ይወስደዋል? 🏆❓

🏆 ወይስ Mubariki 🏆?

✍️ ጨዋታዎቹ ዕለተ እሁድ ጳጉሜ1/2018 ስታድየም በድምቀት ይካሄዳሉ

✍️ ስፖርት ወዳድ የሆናችሁ መላውማህበረሰብ ስታዲየም በመገኘት ይህንን ታሪካዊ የፍፃሜ ጨዋታ እንድትታደሙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል!

🏆🏆

02/09/2026

01/09/2026

/12/2018M.D

3:00 Godo'le
✍️ T/Donibosko Vs Selam

5:00 Godo'le
✍️ A/Korocha Vs Saafa

Category

Website

Address

Daarra
Dilla

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daarrate Woradi Wo/Tu/Ispoortete Borro mini Tuqu Xaadooshshi qola posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Dilla.