Million Bifato Hidano
እግዚአብሔር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ መርጦናል
01/10/2026
!
on your new Job !
may this new chapter
bring your success,
growth and greater achievements .
30/09/2026
soon ❤️❤️ዶ/ር መሳይ
12/09/2026
ዳዬ በንሳ ብዝነስ ግሩፕ ኅ/የተ/የግ/ማህ (አሰፋ ዱካሞ) ለሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ግንባታን ለመደገፍ ቃል የገቡትን ገንዘብ 10 ሚልየን ብር ሙሉ በሙሉ ገቢ ስላደረጉ የፕላትንየም ደረጃ እውቅናና የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ስለ ፍቅር በፍቅር እናሰግናለን
15/06/2026
Maganinke❤️Saali yine Agaroyi Bayicho Cumishiishawo Galatu Laalcho❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️Ayiri Hegerera Magano!!
01/06/2026
ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው፤
ተመራጩ ይህን ታላቅ ህዝብ እንዴት አገልግለው ህይወቱን ይቀይራሉ የሚለው ጉዳይ ይበልጥ ያሳስበኛል።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል
29/05/2026
✔የጨቤ ጋምቤልቱ ወረዳ ሥራ አስፈፃሚዎች በእውነቱ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል🙌 በርካታ ምሁራን ወጣቶች ዛሬ ግን ለ 100 በላይ ሥራ አጦች ቅጥር እየተፈፀመላቸው በመሆኑ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን🙌 መሪዎቻችንን ክፉ አይንካቸው🙌 ዘመናቸው ይባረክ🙌ለተቀጣሪ ወንድሞችና እህቶች ደግሞ እንኳን ደስ አላችሁ🙌 የለቅሶአችሁ ወራት አልፎ የሳቅ ዘመን ስለመጣላችሁ ደስ ብሎኛል እያልኩኝ ሕዝባችሁን በቅንነትና በታማኝነት ከሙስና በፀዳ አእምሮ እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ።
# ለወረዳችን ሥራ አስፈጻሚዎች አደራ ማለት የምፈልገው🙏 ድንገት መረጃ ሳይደርሳቸው የቀሩ ተመራቂዎች ሊኖሩም ስለሚችሉ ይህ መልካምነታችሁ ይቀጥላል የሚል እምነት አለኝ።
daga raare macciisha yaa togooti. sirchi'ne buddeena hooge hudiroonke yesuusi su'minni🙌❤❤❤❤❤
22/05/2026
በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልሎች አቅራቢያ ባሉ የድንበር አካባቢዎች እየተከሰተ ያለው ሁከት፣ የሰዎች ሞት እና የንብረት ውድመት እጅግ አሳሳቢ እና ልብ ሰባሪ ነው። እንዲህ ያሉ የሃይል ድርጊቶች በአስቸኳይ መቆም አለባቸው። ንጹሃን አርሶ አደሮች እና ሲቪሎች በአስተዳደር ክፍተቶች ወይም ባልተፈቱ የአካባቢ ውዝግቦች ምክንያት መቼም ቢሆን ዋጋ ሊከፍሉ አይገባም። ሁለቱም የክልል መንግስታት እና የፌደራል ባለስልጣናት የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ለመጠበቅ፣ እንዲሁም ደህንነትን ለማረጋገጥና ግጭቱ ይበልጥ እንዳይባባስ ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃዎችን የመውሰድ ህገ-መንግስታዊ እና የሞራል ሃላፊነት አለባቸው።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዘላቂ ሰላምን በሃይል ብቻ ማምጣት አይቻልም። ከሁለቱም ወገን ያሉ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና የተከበሩ ግለሰቦች በአንድነት በመቀመጥ የገጭቱን መንስኤዎች መወያየት እና ለትውልዶች አብረው በኖሩት ጎረቤት ማህበረሰቦች መካከል ያለውን እምነት እንደገና መገንባት ይኖርባቸዋል። በሁከቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ እርዳታ እና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በአስቸኳይ ያስፈልጋቸዋል። ከሁሉም በላይ፣ የሰው ልጅ ህይወትን መጠበቅ እና ሰላማዊ አብሮነትን መልሶ ማምጣት ከማንኛውም ሌላ ጉዳይ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
05/05/2026
መዝሙር 121 (Psalms)
7፤ # እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።
Barra Hachumo'ne!!
02/05/2026
የክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሺፈራው ሹጉጤ ቤተሰብ ዛሬ ደማቅ ታሪክ ሰርቷል!🎉 ለሀገራቸው በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው መስክ ትልቅ አሻራ ያሳረፉት አምባሳደሩ፣ ዛሬ ደግሞ በምሳሌነት የሚጠቀሱ ልጆችን ለታላቅ ማዕረግ በማብቃት የእጥፍ ድል ባለቤት ሆነዋል። ልጆቻቸው ዶ/ር አማኑኤል እና ኢንጅነር ምንቴ ከፍተኛ ትምህርታቸውን በስኬት አጠናቀው ለምርቃት መብቃታቸው ተሰምቷል። ይህ ስኬት ለቤተሰባቸው ብቻ ሳይሆን፣ ጠንካራና ባለራዕይ ትውልድ ለሚመኝ ወገን ሁሉ ታላቅ ኩራትና አርአያ ሆኖ ተመዝግቧል። ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሺፈራው ሹጉጤ፣ ለሀገር የሚተርፉ ቁምነገረኛ ልጆችን ለዚህ ማዕረግ ስላበቁ እንኳን ደስ አለዎት እንላለን፤ ተመራቂዎቹም በሙያቸው ለሀገራቸው ብርሃን እንዲሆኑ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን።
01/05/2026
Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስተዳደር
መሠረተ-ልማቶችን ፊትሃዊ በሆነ መልኩ መጠቀም የማንኛውም ሀገር ዜጋ ሊገሰስ የማይችል መሠረታዊ መብት ነው። ይሁን እንጂ በዳዬ ከተማ አስተዳደር የሚስተዋለው ተደጋጋሚና ረጅም ሰዓት የሚወስድ የኃይል መቆራረጥ የህዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከባድ እያደረገው ይገኛል።
#ዋና ዋና ተጽዕኖዎች፦
የንግድ እንቅስቃሴዎች፦ መብራት በዋናነት ለስራቸው የሚጠቀሙ አነስተኛና ከፍተኛ ተቋማት ስራቸውን ማከናወን ተስኗቸዋል።
ማህበራዊ አገልግሎቶች፦ የጤና ተቋማትና የውሃ አቅርቦትና ባንክ በማብራት መቆራረጥ ምክንያት ከፍተኛ መስተጓጎል እየገጠማቸው ነው።
የተማሪዎች ትምህርት፦ ተማሪዎች በምሽት ለማጥናትና ስራዎቻቸውን ለመስራት ተቸግረዋል።
"የዜጎችን ጩኸት መስማትና ለአገልግሎት መቆራረጥ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል"
የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም ሆነ የየደረጃው የሚገኙ የክልላች ኤሌክትሪክ አግልግሎት ቢሮ ነውና ዳዬ ኤሌክትሪክ ማዕከል ፣ የዳዬ_በንሳ ከተማ ህዝብ እያሰማ ያለውን ቅሬታ ሰምታችሁ ዘላቂ መፍትሄ እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
Contact the business
Website
Address
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Million Bifato Hidano posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.